Wickr ደህንነቱ የተጠበቀ ክፍት መዳረሻ

7/9/2018 - 1 ደቂቃ ንባብ

የተሻሻለው: 26/10/2021

Psiphon አዲስና አስደሳች አጋርነትን በማብሰሩ ኩራት ይሰማዋል። ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ደህንነታቸው ለተጠበቁ የመልዕክት መላኪያ መድረኮቻቸው አዲስ ገጽታን ለመፍጠር ከWickr ጋር በጋራ ስንሰራ ቆይተናል፦

Wickr: ደህንነቱ የተጠበቀ ክፍት መዳረሻ።

በዚህ ገጽታ አማካኝነት Wickr እና Psiphon በየትኛውም የዓለም ክፍል — US፣ አውሮፓ፣ እስያ ወይም ላቲን አሜሪካ — ላሉ ቡድኖችና ድርጅቶች ያለምንም የአገልግሎት መቋረጥ አስተማማኝ ከጫፍ-እስከ-ጫፍ የተመሰጠረ የመልዕክት ልውውጥ፣ የስልክ ጥሪ፣ የፋይል እና የስክሪን መጋራትን እንዲያገኙ አስችለዋል። በዚህ መልኩ በየትኛውም የዓለም ክፍል ያልተገደበ ግንኙነትን የሚያስችል ሌላ ምንም አይነት ደህንነቱ የተጠበቀ የመገናኛ መድረክ የለም።
Wickr ሁለገብ በሆነው መድረኩ ደህንነቱ በተጠበቀ የመልዕክት መላኪያ መስክ ላይ በደንብ የታወቀ ሲሆን፣ ድርጅቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ዓለም አቀፋዊ እየሆኑ ሲመጡ በመላው ዓለም ላሉ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነትን ለማረጋገጥ በሚሞከርበት ጊዜ የደህንነትም ሆነ የተደራሽነት ስጋቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገንዝቧል።

Wickr የመጨረሻ ተጠቃሚዎቹ የትም ቢሆኑ ከስራ ባልደረቦቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው ወይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ስለመገናኘት መጨነቅ እንደሌለባቸው ያምናል፤ Psiphonም በዚህ ይስማማል።

የPsiphonን የረቀቁ የኔትወርክ ፕሮቶኮሎችን በአዲሱ ገጽታቸው ውስጥ በማካተት፣ Wickr የመጨረሻ ተጠቃሚዎቹ ትራፊካቸውን ያለምንም እንከን እንዲጠብቁ እና በPsiphon ኔትወርክ በኩል እንዲልኩ ያስችላቸዋል፤ ይህም የትም ቢሆኑ ሁልጊዜ እንደተገናኙ እንዲቆዩ ያደርጋል።

ስለ አዲሱ አጋርነታችን ተጨማሪ መረጃ እዚህ ማንበብ ይችላሉ።
የኩባንያ ዜና

ቀጥለው ያንብቡ