Psiphon ሌላ የሦስተኛ ወገን የደህንነት ግምገማ አጠናቀቀ
16/2/2018 - 2 ደቂቃ ንባብ
የተሻሻለው: 4/6/2021
በሰኔ 2017 መጨረሻ ላይ Psiphon ለአገልግሎቶቻችን የደህንነት ኦዲት እንዲያደርግ Cure53ን በመመደብ ለክፍት ምንጭ ሶፍትዌር ልማት ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጡን ቀጥሏል (የኮድ ማከማቻችንን እዚህ ማግኘት ይችላሉ)፣። የደህንነት ግምገማው “ሰፊ ሽፋን” ያለው ግምገማ ተብሎ የተገለጸውን ለማጠናቀቅ 22 ቀናት እና በድምሩ 9 መርማሪዎችን የወሰደ ሲሆን የ Cure53 መርማሪዎችም በጣም ጥልቅ ነበሩ። ይህ በ3 ዓመታት ውስጥ የዚህ ዓይነቱ 2ኛ የደህንነት ኦዲታችን ነው (በ iSec የተከናወነውን የ1ኛውን ውጤት እዚህ ማየት ይችላሉ)።
በሽፋኑ ውስጥ ምን እንደተካተተ የሚያሳየው የሪፖርቱ መግለጫ እንዲህ ይነበባል፡
“በሽፋኑ ውስጥ የመሿለኪያ-ኮር ደንበኛን እና አገልጋይን፣ የቤተ-መጽሐፍት ማገናኛን፣ የPsiphon iOS መተግበሪያን እና በመጨረሻም የPsiphon iOS አሳሽን ጨምሮ በርካታ የPsiphon ሶፍትዌር ውህድ ክፍሎች ተካተዋል። ይህ በጣም ሰፊ የሆነ መነሻ እና ሽፋን በተለያዩ መስኮች ተገቢ የሆነ እውቀት ያላቸውን በርካታ መርማሪዎችን የማሳተፍ አስፈላጊነትን ያስረዳል። በአጠቃላይ ፈተናዎቹ የኮድ ኦዲቶችን፣ ትክክለኛ የዘልቆ መግባት ሙከራዎችን፣ የስርዓተ-ደንብ እና የውቅረት ግምገማዎችን እንዲሁም የክሪፕቶግራፊክ ኦዲትን ያካተቱ ነበሩ።"
በደህንነት ኦዲቱ ውጤት በጣም ደስተኞች ነን እንዲሁም “ምንም ሊጠቀስ የሚችል የደህንነት ስጋት ሊገለጥ አልቻለም” (ገጽ 19) በማለት ለማስተላለፍ እንኮራለን። በግልጽነት መንፈስ ሙሉውን ዝርዝር ሪፖርት በ pdf ቅርጸት እዚህ ማንበብ ይችላሉ። ከተገኙት ሁለት ተጋላጭነቶች መካከል አንዱ አስቀድሞ የተስተካከለ ሲሆን (እና በ Cure53 የተረጋገጠ)፣ ሌላኛውን ደግሞ በሚቀጥሉት እትሞች ላይ ለመፍታት እርምጃዎች ተወስደዋል።
መርማሪዎቹ በሪፖርቱ ውስጥ ተዘርዝረው ሊያገኟቸው የሚችሉ ሌሎች 7 ልዩ ልዩ ጉዳዮችንም የጠቀሱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አራቱ አስቀድመው ተስተካክለዋል።
“መርማሪዎቹ የሶፍትዌር ውህዱ ባለፈው ጊዜ ከተደረጉ በርካታ የሶፍትዌር ደህንነት ኦዲቶች በእጅጉ እንደተጠቀመ እምነታቸውን አካፍለዋል። ይህም በግኝቶቹ ላይ እንደተንጸባረቀ መናገር አያስፈልግም። በአጠቃላይ ከተገኙት ዘጠኝ ጉዳዮች መካከል ሁለቱ ብቻ እንደ ደህንነት ተጋላጭነቶች የተመደቡ ሲሆን በተጨማሪም ዝቅተኛው የ“መረጃ ሰጪ” አደገኛነት ደረጃ ተሰጥቷቸዋል።”
የCure53 መርማሪዎች በሪፖርቱ ውስጥ ኮዱ ምን ያህል ንጹህ እና በጥራት ላይ ያተኮረ መሆኑን ደጋግመው የገለጹ ሲሆን ወደሚከተለው መደምደሚያም ደርሰዋል፡
“ጥሰት ለመፈጸም ከፍተኛ ጊዜ እና የሰው ኃይል ሀብት ቢወጣም፣ በሽፋኑ ውስጥ ያሉት የPsiphon ክፍሎች ምርመራውን ተቋቁመው በአጥፊ ሙከራዎች ፊት ጠንካራ እና ብርቱ ሆነው ቀርበዋል። ዋናው ቁምነገር ምንም ሊጠቀስ የሚችል የደህንነት ስጋት ሊገለጥ አልቻለም።”
ይህ ሪፖርት ሳቢ ሆኖ እንደሚያገኙት፣ እና ሁልጊዜም ክፍት ምንጭ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አንደኛ ደረጃ ሶፍትዌር ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት እንደሚያረጋግጥልዎት ተስፋ እናደርጋለን።